እንኳን ወደ Leljoch.com በደህና መጡ
ጤና ይስጥልኝ፣ እኔ የleljoch.com ባለቤት በሱፍቃድ ደበበ ነኝ!!
በእዚህ ለኢትዮጵያ ልጆች ተረቶችን ጨምሮ የተለያዩ አእምሮን ለመበልጸግ የሚረዱ ጫወታዎች የሚለቀቁበት ድህረ ገጽ ላይ ስለተገኙ ከልብ ደስ ብሎኛል፡፡
አላማዬ ልጆች የማንበብ ፍቅር እንዲይዛቸው ማድረግ እና በዚህ ቴክኖሎጂ ሁለንተናችንን በተቆጣጠረበት ዘመን ምናቡን መጠቀም የሚችል ትውልድን ማፍራት ነው፡፡
ይህንንም ለማድረግ፡
• ከአለም ዙሪያ አስተማሪ እና ጠቃሚ ናቸው ብዬ የማምንባቸውን ተረቶች ለኛ ሀገር ህጻናት በሚመጥን መልኩ እየተረጎምኩ፣
• ስንዋረስ ያቆየናቸውን ተረቶችም አስፈላጊ ከሆነ በጥቂቱ እያሻሻልኩ ካልሆነም እንደነበሩ እየለጠፍኩ፣
• ለህጻናት ተረት አጻጻፍ ዙሪያ በወሰድኳቸው ስልጠናዎች እና የዉጪ ተረቶችን ስተሮጉም ባገኘሁት ድፍረት እና የራስ መተማመን ተመርቼ ደግሞ የራሴን ተረቶች ለህጻናት በመፍጠር ነው፡፡
• በተጨማሪም ከ3ኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ያሉ ህጻናት የሚማሯቸውን ትምህርቶች የመማርያ መጽሀፎቻቸው ላይ ከተብራሩበት በተሻለ መንገድ ፎቶዎች እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቪድዮዎችን በመጠቀም በማብራራት በትምህርታቸውም የተሻለ ሆነው እንዲገኙ ለማድረግ እሰራለሁ፡፡
ስለ እኔ በጥቂቱ
ተወልጄ ያደኩት በአርባምንጭ ከተማ ሲሆን፣ በሙያዬ የኪነ-ህንጻ ባለሙያ እና በዛው ባደኩበት ከተማ ዉስጥ በሚገኘው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነኝ፡፡
ልጅ እያለሁ ከመኖሪያ ቤታችን ፊት ለፊት የተገነባው ቤተ-መጻህፍት ለንባብ ፍቅር አሳድሮብኝ ያደግኩ ሲሆን ተረቶችን ማንበብ ከልጅነት ዘመኔ ከምወዳቸው ትውስታዎች አንዱ እና ዋነኛው ነው፡፡
የቤተ መጻህፍቱ መሰራት ይህንን ተጽእኖ ያሳደረው በኔ ላይ ብቻ ሳይሆን በአብዛኞቹ የሰፈሬ ልጆች ላይ ስለነበር አሁን ድረስ ከነርእሶቻቸው የምናስተውሳቸው ብዙ የህጻናት መጻህፍቶች እና ተረቶች አሉን፡፡
አሁን ግን ብዙ የከተማዬ ልጆች የህዝብ ቤተ-መጻህፍት መኖሩን እንኳን የሚያውቁት አጠገቡ ያለውን wifi ለመጠቀም ስሩ ተቀምጠው ሰው ሲነግራቸው ነው፡፡ ለነገሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየሰፈሩ እና
በየቤቱ ኢንተርኔት ስለገባ እሱም ቀርቷል፡፡
ስለዚህ ቴክኖሎጂን በቴክኖሎጂ ለመፋለም በማሰብ ይህንን ድህረ ገጽ ሐምሌ 8፤ 2016 ዓ.ም አበልጽጌ ለቀኩት፡፡
ህጻናትን ለማስተማር እና የአእምሮአቸውን እድገት ለማፋጠን ተረቶች እንዲያነቡ ማድረግ እና ሲቻልም አብሮ ማንበብ በተጨማሪም የአእምሮአቸውን የተለያዩ ክፍሎች እንዲያሰሩ የሚያደርጓቸውን ጨዋታዎች ማጫወት በሳይንስ የተረጋገጡ እጅግ በጣም ዉጤታማ መንገዶች ናቸው፡፡
ምናባቸውን የመጠቀም እና የመማር ፍላጎታቸውንም የማሳደግ አቅማቸው ከፍተኛ እንደሆነ በብዙ ጥናቶች ተረጋግጧል፡፡
በዚህ አሉታዊ ተጽእኖ ያላቸው አጫጭር ቪዲዮዎች እና ትርጉም አልባ የስልክ ጨዋታዎች የህጻናትን የትኩረት አቅም (Attention Span) አቀንጭረው በጨረሱበት ዘመን ልጆቻችንን የመታደግ ሃላፊነት እንዳለብን ጽኑ እምነት አለኝ፡፡
እዚህ ድሀረ ገጽ ላይ ምን ያገኛሉ
በአማርኛ የተጻፉ እና በብዛትም እያደጉ የሚሄዱ ተረቶችን በድህረ-ገጻችን ላይ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ልጆት የወደዳቸውን/ቻቸውን ወይንም ለልጆት ይስማማሉ ብለው ያሰቧቸውን ተረቶች ሰብስበው ለብቻ የሚያስቀምጡበት ስርአት ዘርግተናል፡፡
- ተረቶቹ እየተተረኩ ይቀርባሉ
ይህ ማየት የተሳናቸው ህጻናትን ለማካተት እና ከማንበብ ይልቅ ማዳመጥ ለሚመርጡ ህጻናትም እንዲጠቀሙት ታስቦ የተሰራ ነው፡፡ በተጨማሪም ትረካውን እያዳመጡ ጽሁፉን ማንበብ የልጆችን የንባብ ክህሎት የማጎልበት ጥቅም አለው፡፡
- አስደሳች፤ አስተማሪ እና ለአእምሮ እድገት ጠቃሚ መሆናቸው የተረጋገጡ ጌሞችን እንለቃለን
በቅርቡ ደግሞ፡
- አስደሳች፤ አስተማሪ እና ለህጻናት የአእምሮ እድገት ጠቃሚ መሆናቸው የተረጋገጡ ተጨማሪ ጌሞችን እንለቃለን
- እንደ አስፈላጊነነቱ ከወላጆች በሚሰጡን አስተያየቶች ላይ በመመርኮዝ አዳዲስ ነገሮችን እንጨምራለን
- ለልጆች የተለያዩ የቤት ስራዎች እና የOnline ፈተናዎችን በማዘጋጀት እየመዘንን ዉጤታቸውን ከሰጡት መልስ ጋር ለወላጆች በኢሜይል የሚልክ ስርአት በመዘርጋት ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ሁኔታ በተሻለ ቅርበት እንዲከታተሉ እናስችላለን፡፡
- አጋሮችን በመፈለግ ከአማርኛ በተጨማሪ በሌሎች የሀገራችን ቋንቋዎች አገልግሎት እንጀምራለን!
የሌሎችን ስራ ስለማክበር
ሁሉም የ Leljoch.com ላይ የሚገኙ ተረቶች እና ማንኛውም አይነት ስራዎች ወይ በኔ የተፈጠሩ፣ ካልሆነም ደግሞ የማንንም የcopy right መብት በማይጣረስ መልኩ የህዝብ
ግዛት (public domain) ዉስጥ የሚገኙ ስራዎችን በማደስ ወይንም እንዳሉ የተለጠፉ ናቸው፡፡
የግለሰብ ስራዎችን ካለፍቃድ ፈጽሞ አንጠቀምም፡፡
ስራዎቻችንን ለግለሰብ ጥቅም እና ለክፍል ዉስጥ መማማሪያ መምህራን እንዲጠቀሟቸው ታስበው የተሰሩ ሲሆን ለንግድ አገልግሎት እና ለሌሎች ትርፍ አስገኚ ነገሮች ሊጠቀሟቸው ከፈለጉ በ፡
ስልክ ቁጥር: +251 704 409784፣ +251 926409784 ይደዉሉልን፣ ወይንም
Email: leljoch@leljoch.com ይጻፉልን::
የግላዊነት ፖሊሲ
Leljoch.com ላይ የሚያገኙትን አገልግሎት ለማሳለጥ ስም እና ኢሜይል ብቻ ተጠቅመው መለያ እንዲከፍቱ ይጠየቃሉ፡፡
መረጃዎት ደህንነቱ የተጠበቀ ሲሆን፣ ለብዙ ሰዎች ኢሜይል የመላኪያ አገልግሎት ከሚሰጡ እና በዘርፉ የተከበሩ ከሆኑ ድርጅቶች በስተቀር ለምንም አይነት ሶስተኛ አካል አናጋራውም፡፡
ለእነዚህ አካላት መረጃዎትን የምናጋራው በየጊዜው የምንልካቸውን መልእክቶች እርሶ ዘንድ እንዲያደርሱልን ነው፡፡ ካልፈለጉ ከእነዚህ አገልግሎት መረጃዎትን ማንሳት ይችላሉ፡፡
የአገልግሎት ክፍያ
ጠቀሜታቸው በገንዘብ የማይተመን ቢሆንም ለልጆች ተብለው ከሚሰሩ ስራዎች ገንዘብ ማግኘት እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡
ስለሆነም የድህረ ገጹን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ወርሃዊ ክፍያ 150 ብር ብቻ የምንቀበል ይሆናል፡፡
ድህረ ገጹ ላይ አዲስ መለያ ሲከፍቱ ከአጋሮቻችን የአንዱን መለያ ኮድ ካስገቡ ያ አጋር እርሶ እና ሌሎች ያስመዘገባቸው ሰዎች በየወሩ 150 ብር በከፈሉ ቁጥር 50 ብሩ ታሳቢ ይደረግለታል፡፡
ይህ አሰራርም ለብዙ ሰዎች ጥሩ የገቢ ምንጭ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
አጋር መሆን ከፈለጉ በነጻ መለያ ይክፈቱ እና አጋር መሆኛውን ቅጽ በመሙላት ስራ መጀመር ይችላሉ፡፡
የ Leljoch.com ቤተሰብ ስለሆኑ ከልብ እያመሰገንኩ ልጆትም ከድህረ ገጹ የሚገባውን ጥቅም እንደሚያገኝ/ታገኝ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡