ምናገባህ እና አእምሮ
በአንድ አካባቢ ከእናታቸው ጋር አብረው የሚኖሩ ሁለት ልጆች ነበሩ።
የአንዱ ልጅ ስም ምናገባህ ሲሆን የሌላኛው ልጅ ስም ደግሞ አእምሮ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን እናታቸውን ስላመማት አእምሮ አብሯት ገበያ ወዳለው ሱቃቸው ሄዶ ስራ እንዲያግዛት; ምናገባህ ደግሞ ትምህርት ቤት ሄዶ እንዲመዘገብ ተስማምተው ተለያዩ።
ምናገባህ ከእናት እና ወንድሙ ተለይቶ ትምህርት ቤት በመሄድ የሚመዘግበው መምህር "ስምህ ማነው?" ብሎ ሲጠይቀው;
"ምናገባህ!" ብሎ መለሰለት። አስተማሪው ግራ በመጋባት በድጋሚ...
"ስምህ ማነው አንተ ልጅ?" ብሎ ጠየቀው
አሁንም "ምናገባህ!" ብሎ ሲመልስለት ጊዜ መምህሩ በመገረም
"ይሄ ልጅ አእምሮ የለውም እንዴ?" አለ
ይሄን ጊዜ ምናገባህ ፈጠን ብሎ
"አእምሮማ ከእናቱ ጋር ገበያ ሄዷል!" ብሎ እርፍ!