leljoch.com Logo

LELJOCH.COM

ጤና ይስጥልን! ድህረ ገጻችንን ለመጠቀም በመለያ መግባት አለቦት፡፡

በመለያ ለመግባት ወይንም አዲስ መለያ ለመፍጠር እስክሪኖ ላይ በስተግራ ጥግ ከፍ ብለው የሚታዩትን ሶስት ብርትኳናማ መስመሮች ይጫኑ!


የግላዊነት ፖሊሲ

የውሃ ኡደት (Water cycle)

እንዴት ናችሁ ልጆችዬ? መምህርት ኤደን ነኝ!
Teacher Eden: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች
ዛሬ እጅግ በጣም አስደናቂ የሆነ ነገር ላስተምራችሁ ነው።

በየቀኑ የምንጠቀመው ውሃ ከየት እንደሚመጣ, እንዴት እንደሚመረት አስባችሁት ታውቃላችሁ?

ካላወቃችሁ ዛሬ ላሳውቃችሁ ነው! ስለዚህ አብራችሁኝ ቆዩ እሺ!
Kids playing with water: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች
ጸሀይ በምድር ላይ ስታበራ እና ስታቃጥለን እንስሳት እና ሰዎች ሮጠን እንጠለላለን ከፈለግን ደግሞ ሻወር እንወስድና ቅዝቅዝ እንላለን አይደል? 

ባህር, ወንዝ, ሀይቅ እና ሌሎችም የውሃ አካላት ግን የትም ስለማይሄዱ የጸሀይ ብርሃን በደንብ ያቃጥላቸው እና እየተነኑ እንደ ጭስ ሆነው ወደ ሰማይ መሄድ ይጀምራሉ።
Water evaporaton: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች
ልጆችዬ? ትነት በእንግሊዝኛ Evaporation ተብሎ ነው እሺ የሚጠራው ሲነበብ ደግሞ

"ኢ ቫ ፖ ሬ ሽ ን" ተብሎ ነው!

አያችሁት ውሃው እየተነነ ወደሰማይ ሲሄድ?

ከዛን በኋላ የተነነው ውሃ ወደ ሰማይ ወጥቶ ወጥቶ እየተጠራቀመ ጥጥ የመሰለ ነጭ ጉም ወይንም ደመና ይሰራል። 
White cloud: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች
ከዛ አሁንም መሬት ላይ ያለው ውሃ እየተነነ ሲሄድ ሰማይ ላይ ያለው ደመና በጣጣጣጣጣም ተጠራቅሞ ይበዛና ሲቀዘቅዝ ጊዜ ተመልሶ ውሃ መሆን ይጀምራል። 
: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች
በሙቀት ተኖ ጭስ የሆነው ውሃ በቅዝቃዜ ተመልሶ ውሃ ሲሆን በእንግሊዘኛ Condensation ይባላል። አነባበቡ ደግሞ
"ኮ ን ደ ን ሴ ሽ ን" ተብሎ ነው እሺ ልጆችዬ!

ከዛም ከጭስነት ቀዝቅዞ ደመና የሆነው ውሃ አሁንም ሲቀዘቅዝ ዝናብ ይሆን እና ወደምድር ይዘንባል!
Raining: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች
ደመናው በጣም ከቀዘቀዘ በረዶ (በእንግሊዝኛ Snow) ሆኖ ሲዘንብ...
Snow: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች
እጅግ በጣም ከቀዘቀዘ ደግሞ ጠጣር በረዶ (በእንግሊዝኛ Hail) ሆኖ ይዘንባል።
Hail: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች

ከዘነበው ውሃ ግማሹ ተመልሶ ወደ ወንዝ, ሀይቅ, እና ባህር ሲገባ ሌላው ደግሞ ወደ መሬት ውስጥ ይሰርግ እና የመሬት ውሃ ይሆናል! 
Groundwater: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች
የውሃ ጉድጓድ ተቆፍሮ ውሃ ሲቀዳ አይታችሁ አታውቁም? እሱ ማለት ወደ መሬት ሰርጎ የገባው ውሃ ነው ማለት ነው!
Well water: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች
ከዛ የዘነበው ውሃ ተመልሶ በጸሀይ ሲሞቅ ይተን እና ደመና ይሆናል ማለት ነው! እናም የውሃ ኡደት (በእንግሊዝኛ Water Cycle) እንዲህ እያለ ይቀጥላል።
Water cycle: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች
ስለዚህ ልጆችዬ እያንዳንዷ የምታይዋት የውሃ ጠብታ አሰደናቂ ጉዞን አድርጋ ነው እኛጋ የምትደርሰው እሺ!
Water cycle: የአማርኛ ተረቶች: የአማርኛ ተረቶች

ተጨማሪ አዳዲስ ታሪኮች

አእምሮና ምናገባህ: Amharic tales for Children

ምናገባህ እና አእምሮ

ጥጃው ሳምሶን: Amahric story for children

ጥጃው ሳምሶን

የስሜት ህዋሳት ጸብ: Amharic tale

የስሜት ህዋሳት ጸብ

Ethiopian National Flag

የኢትዮጵያ ህዝቦች ብሄራዊ መዝሙር

Teaching about maps

ካርታ ምንድነው?

ዉቢት እና ጭራቁ: Amharic tales for children

ውቢት እና ጭራቁ

ሰባተኛው እና የመጨረሻው የሲንባድ ጉዞ: Amharic tales

ሰባተኛው እና የመጨረሻው የሲንባድ ጉዞ

ስድስተኛው የሲንባድ ጉዞ: Amharic tales

ስድስተኛው የሲንባድ ጉዞ

search

ተረት መፈለግያ